Thursday, 20 Jun 2013
You are here: Home Expresspost (EMS1)
EMS News PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Tuesday, 21 September 2010 06:34

ፈጣን መልዕክት አገልግሎት ኢትዮጵያ
/. ኤም.ኤስ/
World Wide Express Ethiopi a

የደንበኞች ቅድመ መረጃ
Service requirement

መልዕክት ለመላክ

 

  • የመልዕክቱን ክብደት በቅድሚያ ማወቅ ከፈለጉ ይመዝኑ፣
  • መልዕክቱን በግል ፖስታ ወይም ካርቶን በቅድሚያ ማሸግ የተከለከለ ነው፣
  • መልዕክቱ የጉምሩክ ፎርማሊቲ የጤና ጥበቃ ባለሙያ የሚያስፈልገው ከሆነ በቅድሚያ ያሟሉ፣
  • ተሠባሪ ዕቃ ለጊዜው አንልክም የምትልኩ ለሚደርሰው አደጋ ኃላፊነቱን ይውስዳሉ፣
  • ጥራጥሬ እና ያልተፈጨ ቅመማ ቅመም የምትልኩ ደንበኞች የናሙና/Sample/ ፈቃድ ከኮፒ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  • መልዕክቱ ዶክመንት ከሆነ ፍላየር ኤንቨሎኘ፣ ዕቃ ከሆነ እንደመልዕክቱ መጠን ካርቶን ከማስተናገጃ መስኮት ይረከቡ፣
  • መልዕክቱን ባሉበት ወይም ደውሎ ለማደል ያስችል ዘንድ የሚከተሉትን መረጃዎችን በትክክል ይመዝግቡ፣
  • ጽሁፉ እንዲነበብ አድርገው ይጻፉ፣
  • የተቀባይና የላኪ ሙሉ ስም
  • ውጭ አገር የሚልኩ ከሆነ የመንገድ ስምና የቤት ቁጥር፣ ከተማ እና ሃገር፣
  • አገር ውስጥ የሚልኩ ከሆነ የክፍለ ሃገሩን (ከተማ) ስም በትክክል ይመዝግቡ
  • መልዕክቱን በካርቶን ወይም በኤንቨሎኘ ውስጥ በትክክል ከአስገቡ በኋላ ሳያሽጉ መስኮት ላይ ለሚያስተናግዱ ሠራተኞች ያስረክቡ፣
  • የመላኪያ ዋጋ ይክፈሉ፣ የከፈሉበትን ደረሰኝ ይረከቡ፣

መልዕክት ለመቀበል

 

    • ሕጋዊ መታወቂያ፣ ፖስፖርት ፣ መንጃ ፈቃድ ወይም ንግድ ፈቃድ  ያቅርቡ፣
    • የጤና ጥበቃ ባለሙያ የሚያስፈልገው ከሆኑ ያሳዩ፣
    • የጉምሩኩ ቀረጥ የሚያስፈልገው ከሆነ ይክፈሉ፣
    • ተቀባይ ተወካይ ከሆነ ሕጋዊ ውክልና ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በማቅረብ መልዕክቱን ይረከቡ

የማደያ ዋጋ አናስከፍልም

Last Updated on Wednesday, 03 November 2010 10:15