Tuesday, 18 Jun 2013
You are here: Home
91ኛው ዙር መሠረታዊ የፖስታ ዕውቀትና የሂሣብ ሥራ ስልጠና ተጠናቀቀ PDF Print E-mail

ከሚያዚያ 24 - ሰኔ 23 ቀን 2003 ዓ.ም የተሰጠው መሠረታዊ የፖስታ ዕውቀትና የሂሣብ ሥራ ኮርስ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ ስልጠናው የተሰ ጠው አዲስ አበባን ጨምሮ ከ9 የተለያዩ ዞን ፖስታ ቤቶች ለተወ ጣጡ 31 የድርጅቱ ሠራተኞች ሲሆን ሰልጣኖቹ በስልጠና ወቅት ስለደብዳቤ አሰራር፣ ጥቅል፣ ፋይናንሻል ቢዝነስ፣ የኢ.ኤም.ኤስ፣ እና የቤትለቤት ቅበላና ዕደላ ሥራ እና የሂሣብ ሥራና ሪፖርት አቀራረብ በተመለከተ ሰፋ ያለ ትምህርታዊ ስልጠና እንደተሰ ጣቸው የትመህርት ክፍሉ ባለሙያ ወ/ት ፅጌ አለማየሁ አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም ሰልጣኖች ሰፋ ያለ ውይይት ያደረጉ ሲሆን የግንዛቤ ማስጨበጫ ፈተናን ጨምሮ በተለ ያዩ የሥራ ክፍሎች በመዘዋወር የተግባር ዕውቀት ቀስመዋል፡፡ በተጨማሪም  የሁለት ቀናት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና፣ የድርጅቱ እምነቶችና እሴቶች ስልጠና እንደተሰጣቸውም ከስልጠና ክፍሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህም ሰልጣኞቹ ባገኙት ዕውቀት በመደ ሰት ድርጅቱ የተያያዘውን የዕድገት ጉዞ የተሳካ ለማድረግ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ ቃል ገብተ ዋል፡፡ በመቀጠልም የድጋፍ ሰጪ ዘርፍ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታደለ አሰፋ ለሰልጣኞች የምስክር ወረቀት የሰጡ ሲሆን የተሻለ ውጤት በማምጣት ከ1-3 ለወጡ ሰልጣኞች ሽልማት አበርክተዋል፡፡

በመጨረሻም ሰልጣኞቹ በቆይታ ቸው ባገኙት ዕውቀት መሠረት ለደንበኞች የተለየ ትኩረት በማድ ረግ የተሻለ አገልግሎት በመስጠት የባለቤትነት እና የተነሳሽነት ስሜታቸውን ማጐልበት እንዳለ ባቸው እንዲሁም ድርጅቱ በጀመረው የለውጥ ጉዞ የድርሻ ቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል