Afghan Post Afghan PostAfghan Post

 

 
About usEMSLettersParcelsMoney transferPhilatelyTrack & TraceContact

የ2002 ዓ.ም የዓለም ፖስታ ቀን ተከበረ

የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት 169ኛው የዓለም ፖስታ ህብረት የተመሠረተበትን ቀን በሀገሪቱ በሚገኙ 19 ዞን ፖስታ ቤቶች አከበረ፡፡ በተለይ በዋናው ፖስታ ቤት በሀገር አቀፍ ደብዳቤ አፃፃፍ ውድድር ከ1ኛ-3ኛ የወጡ ታዳጊ ወጣቶች ሽልማት በመስጠት ተከብሯል፡፡

በዕለቱ በትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ፒተር ጋትኮት ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ማኔጅመንቱና ሠራተኛው ተጠናክረው በመሥራታቸው ለውጦችን እያስመዘገቡ መሆኑን ጠቅሰው ለቀጣይነትም የበለጠ ውጤት ለማምጣት ተቀናጅተው መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ግደይ ገ/ዮሐንስ  በበኩላቸው ድርጅቱ የህብረቱ አባል ከሆነበት ከ1901 ዓ.ም ጀምሮ ክህብረቱ ጋር የጠበቀ ግኙኝነት እያደረገ መሆኑን ገልጸው እንደሌሎች ፖስታ አስተዳደሮች ተገቢውን የአባልነት ክፍያ በየኣመቱ በመክፈል ንቁ ተሳትፎ እያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ህብረቱም የድርጅቱ አቅም እንዲጎለብት ከሚሰጠው ድጋፍና ስልጠና በተጨማሪ ቀርጾ በሚያቀርባቸው የፖስታ ጥራት ማሻሻያ ፕሮጀክቶች ላይ ድጋፍ በማድረግ ይገኛል፡፡

የ2002 የዓለም ፖስታ ቀን #የዓለም ፖስታ ህብረት ትስስር እንደተጠናከረ ይቀጥል; በሚል መርህ ቃል እየተከበረ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ግደይ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የመሠረታዊ አሠራር ጥናትን ተግባራዊ አድርጎ መንቀሳቀስ ከጀመረ ወዲህ ጥሩ ውጤቶችን እያስመዘገበ እንደሚገኝ ገልጸው ወደፊትም በተግባር ላይ በዋለው አዲስ የፖስታ ልማት ፖኬጅ አቅሙን አጠናክሮ ከአፍሪካ አልፎ በዓለም ተጠቃሽ ወደሚሆንበት ደረጃ እንደሚሸጋገር ግልጸዋል፡፡

   በዕለቱ በሀገር አቀፍ ደብዳቤ አፃፃፍ ውድድር ከ1ኛ-3ኛ የወጡ ታዳጊ ወጣቶች ድርጅቱ ያዘጋጀላቸውን ሽልማት ተቀብለዋል፡፡ በበዓሉላይ የዓለም ፖስታ ህብረት ይሬክተር ሚስተር ኤድዋርድ ደያን #የፖስታ አስተዳደደሮች ለደን ሽፋን ትኩረት ይስጡ; በሚል ርዕስ የፖስታው ኢንዱስትሪ የአየር ብክለትን ለመቀነስ እየሠራ እንደሚገኝ የሚገልጽ መልዕክት ተነቧል፡፡    

የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል ተከበረ

"ስንደቅ ዓላማችን የዴሞክራሲያዊ አንድነታችን መገለጫ ነው!"

ሰንደቅ ዓላማ የሀገራት የሉዓላዊነትና የነፃነት መገለጫ በመሆኑ አገራችን ኢትዮጵያም የራሷ መለያ የሆነ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ሊኖራት ይገባል፡፡ ይህንም ከግምት በማስገባት የሰንደቅ ዓላማ ቀን መስከረም 25 ቀን 2002 ዓ.ም በመላው ሀገራችን ለ2ኛ ጊዜ ተከብሮ የዋለ ሲሆን ድርጅታችንም በዕለቱ ከጥዋቱ 4፡30 -4፡50 በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አክብሯል፡፡

የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር ዴኤታዎች  ክቡር አቶ ጌታቸው መንግሥቴና ክቡር አቶ ፒተር ጋትኮት በኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር በመታጀብ የሰንደቅ ዓላማ አሰቃቀል ሥርዓቱን አከናውነዋል፡፡ ክቡር አቶ ጌታቸው መንግሥቴ የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር የትራንስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በሰንደቅ ዓላማ አከባበር ሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን ሀገር ወዳድ የሆኑ ህዝቦች ከጊዜ ወደ ጊዜ እናት ሀገራቸው ላይ የሚጋረጡ ጠላቶችን ሲመክቱና ከደም ጠብታ እስከ ህይወት መስዋዕትነት ሲከፍሉ የነበሩት ለሰንደቅ ዓላማቸው ክብርና ፍቅር የተነሳ መሆኑን አውስተዋል፡፡ በተጨማሪም የዛሬው ትውልድም ድህነትን በማጥፋቱ ዘመቻ በጽናት በመታገል ሰንደቅ ዓላማችን በኩራት እንዲውለበለብ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

 

በተያያዘ ዜናም በዕለቱ ከቀኑ8፡30 እስከ 9፡30 በፖስታ አገልግሎት ድርጅት ዋና መ/ቤት የሚገኙ ከፊል ሠራተኞች የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓልን አስፈላጊነትና ትርጉም በተመለከተ የፓናል ውይይት አካሂደዋል፡፡

 

 

 


የዋናው መሥሪያ ቤት ካውንተር ሠራተኞች “ለደንበኛ ክብር እንስጥ” በሚል መሪ ቃል የቡና ጠጡ ፕሮግራም አዘጋጁ

ዋናው ፖስታ ቤት የሚገኙ የካውንተር ሠራተኞች በራሳቸው ተነሳሽነት #ለደንበኛ ክብር እንስጥ; የቡና ፕሮግራም በሚል መርህ ተነሳስተው መስከረም 16/2002 ዓ.ም በ2002 ዓ.ም በያዝነው በጀት ዓመት ለደንበኞች መልካም ሥነምግባርን በተላበሰ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ገለጹ፡፡

በዕለቱ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በካውንተር ላይ ለደንበኞች ቡና በመጋበዝ እና ቀርቦም በማነጋገር ከዚህ ቀደም የነበሩ ስህተቶችን አርመው የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አስረድተዋል፡፡

የካውንተር ሠራተኞቹ እርስ በእርስ ግምገማ ያካሄዱ ሲሆን በግምገማው ሂደትም ሠራተኛው አሉብኝ ያላቸውን ችግሮች፣ ከቅርብ ኃላፊዎች ጋር ያለ የግኑኝነት ድክመት እንዲሁም በዞኑና በድጋፍ ሰጪ መካከል የታዩ ችግሮችን በማቅረብ ግልጽ ውይይት እንደተደረገባቸው ገልጸዋል፡፡

ሠራተኞች ለሥራቸው ቅልጥፍና አመቺ የሆኑ ቁሶችና አልባሳቶች እንዲሟሉላቸውም ጥያቄያቸውን አቅርበዋል፡፡

በዕለቱ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ግደይ ገ/ዩሐንስ ሠራተኞች በራሳቸው ተነሳሽነት የፈፀሙት ተግባር ሊበረታታ እንደሚገባው ገልጽው፤ ይህ ድርጅቱ ላሰበውም ዓላማ መሳካት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል፡፡


አመራሮች ተሸለሙ

የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጀት ሠራተኞች በ2001 በጀት ኣመት ድርጅቱ ጥሩ ውጤት እንዲያገኝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ የበላይ አመራሮች በራሳቸው ተነሳሽነት መዋጮ በማሰባሰብ ሽልማት አበረከቱ፡፡

መስከረም 23/2002 በዋናው ፖስታ ቤት በተደረገ ስነስርዓት ለኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጀት  ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ግደይ ገ/ዮሐንስ እና ለድጋፍ ሰጪ ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደለ አሰፋ  እንዲሁም ለሠራተኛ ማህበር ሽልማቱን በትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ድሪባ ኩማ ናቸው፡፡ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር ፖስታ አገልግሎት ድርጅት #ቀይ መብራት; በርቶበት እንደነበር አስታውሰው አሁን ግን መለወጥ እንደሚችል ያሳየ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም በሌላው ዓለም የሚገኙ የፖስታ አስተዳደሮች ዘርፈብዙ አገልግሎት በጥራት እንደሚሰጡና የኢትዮጵያ ፖስታም ወደዚያ ለመድረስ ጥሩ ተስፋ እናዳለው ገልጸዋል፡፡

በዕለቱ የሸላሚው ኮሚቴ ባስተላለፈው መልዕክት ድርጅቱ ከ2001 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፃር ከ100% በላይ እድገት ሊሳይ የቻለው የኢፊዲሪ መንግስት ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠቱ፣ የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር የቅርብ ክትትል በማድረጉ፣ የድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎች በሁሉም የሥራ ክፍል በመገኘት በቅርብ ሆነው የሠራተኛውን ሞራል የሚጠብቅ እገዛ በመስጠታቸው፣ ቦርዱም ገንቢ አቅጣጫ ማሳየት በመቻሉ እንዲሁም የማኔጅመንት አባላት በትጋት መምራት በመቻላቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ይህ በመሆኑም ለዚህ ውጤት ያበቁትን ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ለማመስገን የተዘጋጀ ፕሮግራም እንደሆነ ተገልÍል፡፡የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት አቶ ግደይ ገብረዮሐንስ በበኩላቸው ባስተላለፉት  መልዕክት የተበረከተላቸው ሽልማት ለበለጠ ሥራ እንደሚያነሳሳቸው ጠቅሰው የድርጅቱ ሠራተኛ ከፍተኛ ኃላፊነት እንደጣለባቸው ገልጸዋል፡፡

በፕሮግራሙ ለጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ፣ ለትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር አቶ ድሪባ ኩማ፣ በትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር  ሚኒስትር ዴኤታዎች ለአቶ ፒተር ጋት ኮት እና ለአቶ ጌታቸው መንግሥቴ፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅትየቦርድ ሊቀመንበር ለሆኑት ለአቶ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የተለያዩ ሽልማትቶች ከሠራተኛው ተበርክቷል፡፡

 

 
 
 
 

 

 
 
Enter your 13 Digits here to Track EMS items
a
 

ዲቪ(DV) የደረሳችሁ ዝርዝር

   

  Login Name:
Passowrd:
Changepassword
For technical assistance or comments, please contact webmaster@ethiopostal.com .
© 2009 ethiopian post
Free Hit Counters
HTML Hit Counters